Ethiopia's PM Hailemariam Desalegn speech on Parliament

Thanks! Share it with your friends!

You disliked this video. Thanks for the feedback!

Ethiopia's Prime Minister Hailemariam Desalegn speech at a Parliament

Category
Politics Ethiopian News

Added by bini
43,448 Views

Post your comment

Comments

 • ኢሳ
  Added

  የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና አሁን ለአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት የሚወዳደሩት የህወሃቱ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሸዋ እና በአርሲ ዞኖች ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ገዝተው የቲማቲም እርሻ እያኬዱ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ እና በዋና ዋና የአገሪቱ ከተሞች የታየውን የቲማቲም እጥረት ተከትሎ፣ ከፍተኛ ገቢ እያገኙ ነው።
  በአዲስ አበባ የቲማቲም ዋጋ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ያሻቀበ ሲሆን፣ 1 ኪሎ ቲማቲም እስከ 45 ብር ይሸጫል።ቲማቲም አምራች በሆኑ አካባቢዎች የኪሎ ቲማቲም ዋጋ 35 ብር ደርሷል
  አንድ ሊትር የቲማቲም ፀረ-ተባይ መድሃኒት 12 ሺህ ብር እየተሸጠ ነው

  ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቲማቲም ተክል ላይ የተከሰተውና ቱታ አብስሉታ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ወረርሽኝ የቲማቲም ተክልን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ሊያጠፋው ይችላል የሚል ስጋት መፍጠሩ ተነገረ፡፡ በአንድ ጀንበር የቲማቲም ማሳውን ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት ይችላል ተብሎ የተፈራው ወረርሽኙ፤በሀገሪቱ ዋና ዋና ቲማቲም አብቃይ አካባቢዎች መከሰቱንና ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑም ተገልጿል፡፡ በወረርሽኙ መከሰት ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው የቲማቲም አምራች አርሶ
  አደሮች አንዱ እንደሚናገሩት፤ከዓመታት በፊት በአካባቢው ያለ ምንም ፀረ-ተባይ መድኃኒት የቲማቲም ምርት ማምረት ይችሉ ነበር፤አሁን ግን በተለይም በያዝነው የምርት ወቅት የተከሰተው ወረርሽኝ ማሳውን ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ እንዳደረገባቸውና በዚህም የተነሳ ከፍተኛ ኪሳራ ላይ መውደቃቸውን ገልፀዋል፡፡ “በ8 ሄክታር ላይ ያመረትኩት ቲማቲም ከጥቅም ውጪ በመሆኑ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር የገንዘብ ኪሳራ
  ደርሶብኛል” ብለዋል – አርሶ አደሩ፡፡ ለአዲሱ ወረርሽኝ መድኃኒት ነው እየተባለ አንዱን ሊትር በ12 ሺህ ብር እየተገዛ የሚረጨው ጸረ-ተባይም በአብዛኛው የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈና ምንም ዓይነት መድሃኒትነት የሌለው ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ባለፈው እሁድ በአዳማ ከተማ የተከበረውን 8ኛውን የአርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ቀን ምክንያት በማድረግ የግብርናና የእንስሳት ሀብት
  ሚኒስቴር ለጋዜጠኞች አዘጋጅቶት በነበረው የመስክ ጉብኝት፤በምስራቅ ሸዋ ዞን ሎሚ ወረዳ፣ ቆቃ ነገዋ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ ተዘዋውረን የተመለከትናቸው የቲማቲም ማሳዎች በወረርሽኙ ለጥፋት የተጋለጡ ሲሆኑ አምራቾቹም ለከፍተኛ ሥጋት ተዳርገዋል፡፡
  በሥፍራው ያገኘናቸው ቲማቲም አብቃይ አርሶ አደሮች እንደሚናገሩት፤ወረርሽኙ ድንገተኛና በጥቂት ጊዜ ውስጥ ማሳውን ሙሉ በሙሉ ሊያወድም የሚችል መሆኑ ከፍተኛ ሥጋት ላይ ጥሏቸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በሊትር 12 ሺህ ብር እየገዙ በሚረጩት ፀረ ተባይ መድኃኒት ጊዜያዊ
  እረፍት ማግኘታቸውንም አርሶ አደሮቹ ተናግረዋል። ሁኔታው በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ግን በጥቂት ጊዜ ውስጥ የቲማቲም ምርት ሙሉ በሙሉ ከገበያ ሊጠፋ እንደሚችልም ገልፀዋል፡፡ መንግስት ችግሩን ለመቅረፍ ያደረገው ምንም ሙከራ አለመኖሩን የተናገሩት አርሶ አደሮቹ፤የግብርና ኤክስቴንሽን ባለሙያ እየተባሉ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱት ሰዎች በየጊዜው እየመጡ ማሳውን ጎብኝቶ ከመሄድ ውጪ ያደረጉት አንዳችም ነገር የለም ብለዋል፡፡ በምስራቅ ሸዋ ዞን ሎሚ ወረዳ፣ ቆቃ ነገዋ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ የግብርና ኤክስቴንሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ ብርሃነ እሸቴ በበኩላቸው፤ መንግስት ለግብርናው ዘርፍ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት አዳዲስ የቴክኖሎጂ አሰራሮችን ወደ ገበሬው ለማስረፅና ገበሬውን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ በቅርቡ የተከሰተው ቱታ አብሱሉታ የተባለው የቲማቲም ወረርሽኝ ከቁጥጥር ውጪ በመሆን ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን አልሸሸጉም፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት መደረጉን የገለጹት አቶ ብርሃነ፤በኦሮሚያ ግብርና በኩል ኮራጎን የተባለ ፀረ ተባይ መድኃኒት ለአርሶ አደሮቹ እንዲቀርብ
  ተደርጓል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ የግብርናና የእንስሳት ሀብት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ካባ ኡርጌሳን ስለ ጉዳዩ ጠይቀናቸው፣ችግር አለባቸው በሚባሉ አካባቢዎች ላይ የፀረ ተባይ መድሃኒቶች እጥረት መኖሩን ጠቁመው፤አስቸጋሪነቱ እየታየ መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ ሊወስድ ይችላል
  ብለዋል፡፡ አርሶ አደሮቹ መድኃኒቶቹን በውድ ዋጋ እየገዙ መጠቀም ብቻ ሳይሆን የመድኃኒቱን ትክክለኛነትም ማረጋገጥ እንደሚገባቸው ዶ/ር ካባ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
  ይህ “East Africa” የሚል ስያሜ ያለው የዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም እርሻ 120 ቀርጥ ወይም ስፋቱ 30 ሄክታር ሲሆን፣ እርሻው ሙሉ በሙሉ የሚያመርተው ቲማቲም ነው። የቲማቲሙ እርሻ በዘመናዊ መንገድ የአጠና መደብ የተሠራለት ነው። ከእያንዳንዱ ቀርጥ እስከ 4 ቢያጆ ቲማቲም እየተጫነ ወደ አዲስ አበባ በመላክ ላይ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።
  የእርሻ ቦታው በቀድሞ ግዜ በመንግሥት የልማት ድርጅት ስር ውስጥ የነበረ ሲሆን፣ አገዛዙ ለግል ባለሀብቶች ሲሸጠው የዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም ዘመድ የሆነው አቶ ገብረ መስቀል አርአያ ገዝቶት ነበር። ይሁን እንጅ ዶ/ር ቴዎድሮስ ከ2008 ዓ/ም ግማሽ አመት ጀምሮ ተረክበው እየሰሩበት ሲሆን፣ ቀድሞ የነበሩ የድርጅቱን ሠራተኞች ከግማሽ በላይ ተባረው የራቸውን ሰዎች ቀጥረዋል። ከእስራኤል ሀገር የመጡ የእርሻ ባለሙያዎችንም ተቀጥረው በመስራት ላይ ናቸው።
  ከዚህ በፊት ያልነበረ የቲማቲም በሽታ ገብቶ የአካባቢው ገበሬዎች የሚያመርቱትን ቲማቲም ያወደመው ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ለተፈጠረው የቲማቲም እጥረትም ይህ አንዱ ምክንያትም ነው። በበሽታው ያልተጎዳው የዶ/ር ቴዎድሮስ የቲማቲም እርሻ ብቻ መሆኑ፣ የአካባቢውን ህዝብ እያነጋገረ ነው።
  ምንጮች እንደሚሉት በአገሪቱ የቲማቲም በሽታ መድሀኒት ብቸኛ አስመጪ እራሳቸው ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ናቸው። እጅግ ውድ ከሆነው የመድሃኒት ሽያጭ ከፍተኛ ትርፍ እየሰበሰቡ መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ።
  አገሪቱ የቲማቲም እጥረት አጋጥሟት ባለበት ሰአት East Africa ቲማቲም ወደ ጂቡቱ ለመላክ ዝግጅት እያደረገ ነው።


Sponsors